ቅሬታ ያቅርቡ
በሰሜን አሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አልባሳት እና ሌሎች ምርቶችን በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ውስጥ ለሰራተኞች ቅሬታ ምላሽ ለመስጠት ወይም በፋብሪካ ውስጥ ችግር እንዳለ የሚጠቁሙ መረጃዎች ከሌሎች ሲገኙ የሰራተኛ መብቶች ጥምረት የስራ ሁኔታን ይመረምራል። ከዚህ በፊት የተተገብሩ ምርመራዎች ከስራ ቦታ ውጪ፣ ሰራተኞች ምቾት በሚሰማቸው ቦታ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፣ ፣ እንዲሁም ተዛማጅ ሰነዶችን በማሰባሰብ እና ከአመራር እና ከሌሎች የታወቁ ምንጮች ጋር የተደረጉ ንግግሮችን አካተዋል። በፋብሪካ ውስጥ ጥሰቶች ሲገኙ፣ የሰራተኛ መብቶች ጥምረት የማሻሻያ ምክሮችን ይሰጣል።
የሰራተኞች ቅሬታዎች አብዛኛውን ጊዜ ከ የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ሰራተኞች ጋር ግንኙነት ባላቸው መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ወይም በሠራተኛ ማኅበራት በኩል ወደ የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ይመጣሉ። ሆኖም ሰራተኞች ወይም ተወካዮቻቸው ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ በመሙላት ለሰራተኛ መብቶች ጥምረት ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ፡-
እባክዎን የስምዎን እና የአድራሻዎን ሚስጥራዊነት ጠብቀን እንደምናቆይ ያስታውሱ። ከእርስዎ ልዩ ፈቃድ ከሌለን በስተቀር ይህ ሁሉ በማንኛውም ጊዜ አይታተምም። ያቀረቡት መረጃ ቅሬታውን ለመከታተል ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል።
ለሚደርሱት ቅሬታዎች ሁሉ የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ሙሉ ምርመራ አያደርግም። የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ወደ ምርመራ ወስኖ ለመግባት የተለያዩ ሁኔታዎችን ይገመግማል እነዚህም የተጠረጠሩ ጥሰቶች ከባድነት፣ የተጎዱት ሰራተኞች ብዛት፣ ስለ ክሱ ታማኝነት ጉዳዩን የሚያውቁ የአካባቢ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አመለካከቶች፣ ከዩኒቨርሲቲ ጋር ተዛማች የሆኑ ብራንዶቸ ከፋብሪካው ጋር ያላቸው የቁርኝት መጠን ውጤታማ የማስተካከያ መርሃ ግብር ለማዘጋጀት ይረዳ ዘንድ እና ሰራተኞቹ እራሳቸው የምርመራውን ሀሳብ የሚደግፉ መሆናችው ናቸው፡፡