የኡዩጉር የግዳጅ ጉልበት ማብቃት

የቻይና መንግስት በኡዩጉር እና በሌሎች ቱርኪክ እና ሙስሊም - አብዛኛዎቹ ህዝቦች ላይ የሚፈጽመው በደል የሰብአዊነት ወንጀል ተደርጎ ሲቆጠሩ፣ ግንባር ቀደሞቹን አልባሳት እና ቸርቻሪዎች በከባድ የሰብአዊ መብት ቀውስ ውስጥ እያሳተፈ ነው። በመንግስት የሚደገፈው የግዳጅ ሥራ በሺንጂያንግ ኡይጉር ራስ ገዝ ክልል (ኡይጉር ክልል) ውስጥ በስፋት የተስፋፋ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ይጨመራል ከእነዚህም መካከል፡ የጅምላ የዘፈቀደ እስራት፣ የግዴታ የፖለቲካ ትምህርት፣ በግዳጅ ቤተሰብ ማለያየት እና ሰፊ ክትትልን ያካትታል።

የአልባሳትና የጨርቃጨርቅ ዘርፍ የቻይና መንግሥት የግዳጅ ሥራ መርሃ ግብር ማዕከል ነው። በዓለማቀፉ አልባሳት ኢንዱስትሪ ትልቁ ለግዳጅ ሥራ የተጋላጭነት አደጋ በልብስ ስፌት ደረጃ ሳይሆን በጥጥ እና ክር ምርት የአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ የተደነቀረ ነው። የኡይጉር ክልል 20 በመቶው የአለም የጥጥ ምርት ምንጭ ነው፣ ይህ አስደናቂ ስታስቲክስ ቁጥርን ያመለክታል።

 

በአለም አቀፍ የአልባሳት ገበያ ውስጥ ከአምስቱ የጥጥ አልባሳት አምራች ውስጥ አንዱ ከኡዩጉር ክልል ግብአት የሚያስመጣ ሲሆን ይህም በግዳጅ ጉልበት ስራ የመሰራት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

አልባሳት እና ቸርቻሪዎች ለኡዩጉር የግዳጅ ጉልበት ቀውስ አስተዋፅዖ የሚያደርጉት አራት፣ ብዙ ጊዜ እርስ በርስ የሚያያዙ መንገዶች አሉ።

  1. በኡይጉር ክልል ውስጥ ከሚገኙት አልባሳት ወይም ሌሎች ጥጥ ላይ የተመረኮዙ ዕቃዎችን ከሚሠሩ ማናቸውንም የማምረቻ ተቋማት ጋር ባለ የንግድ ግንኙነት፤
  2. በኡይጉር ክልል ውስጥ የሚገኙ ቅርንጫፎች ወይም ሥራዎች ካላቸው እና የቻይና መንግሥት ድጎማዎችን እና/ወይም በመንግሥት የሚቀጠሩ ሠራተኞችን ከተቀበሉ ከኡዩጉር ክልል ውጭ ከሚገኙ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ግንኙነቶችን በማድረግ፤
  3. ከኡዩጉር ክልል ውጭ በሚገኝ የስራ ቦታ፣ በመንግስት የተላኩ የኡይጉር ክልል ሰራተኞች ቀጥሮ ከሚያሰሩ አቅራቢዎች ጋር በሚመሰረት የንግድ ግንኙነት፤
  4. በቻይና ውስጥ ካሉ አቅራቢዎች ጋር እና በአለም አቀፍ ደረጃ ከኡይጉር ክልል የሚመረቱ ግብዓቶች እንደ ጨርቅ፣ ክር ወይም ጥጥ ያሉ አስመጪዎች ጋር ባለ የንግድ ግንኙነት፡፡

በክልሉ ካለው ከፍተኛ የጭቆና እና የክትትል ደረጃዎች የተነሳ ብራንዶች እና ቸርቻሪዎች የአቅርቦት ሰንሰለታቸው ከግዳጅ ጉልበት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች - ማለትም የሠራተኛ መብቶች ኦዲት - በዚህ ሁናቴ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ የማይቻል ነው። ምክንያቱም አንድ ሠራተኛ አጸፋውን ወይም በቀልን ሳይፈራ ከገለልተኛ መርማሪ ጋር በግልጽ መነጋገር ስለማይችል ነው። በመሆኑም የአልባሳት ብራንዶች እና ቸርቻሪዎች በኡይጉር የግዳጅ ስራ ላይ ተባባሪ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ የሚችሉት በየደረጃው ያለውን የአቅርቦት ሰንሰለት ከጥጥ እስከ ጨርቃጨርቅ ድረስ ጥሎ በመውጣት እና በዚህ የግዳጅ የጉልበት ቀውስ የተመላከቱ ድርጅቶች ጋር ያላቸውን የንግድ ግንኙነት ጨረሶ በማቆም ነው።