የኢትዮጵያ ምርመራዎች
ኤቨረስት አፓርል
ደብሊው አር ሲ - WRC በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው በኤቨረስት አፓርል ፋብሪካ ላይ በርካታ ከባድ የሰራተኛ መብት ጥሰቶችን በጥናቱ መዝግቧል። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡- ሕገ-ወጥ የደመወዝ ቅነሳ፣ ሳምንትዊ ዕረፍት ቀን አለመስጠት፣ አስገዳጅ የትርፍ ሰዓት ስራ፣ የቃላት ጥቃቶች፣ የዓመታዊ ፍቃድ ገደቦች፣ የሰራተኞች የመደራጀት መብትን ማፈን እና ደህንነቱ ያልተጠበቀ የፋብሪካ ሙቀት መጠን ናቸው። WRC ግኝቶቹን እና የማሻሻያ ምክረ ሀሳቦቹን ለፈቃድ ሰጪው ለከተር ኤንድ በክ እና የኮሌጅ ያልሆኑ አልባሳትን ከፋብሪካው ለሚውስድው ለዴካትሎን አጋርቷል። ከተር ኤንድ በክ ከኤቨረስት አፓርል ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት እኛ ከፋብሪካው ጋር ውይይታችንን ከመጀመራችን በፊት ማቋረጡን ለ WRC ያሳወቀ ሲሆን ነገር ግን አመራሩ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እስኪወስድ ድረስ ለፋብሪካው የሚከፍለውን የመጨረሻ ክፍያ ለማዘግየት ተስማምቷል።
ከፋብሪካው እና ከፈቃድ ሰጪው ጋር ከተወያየን በኋላ ኤቨረስት ጥሰቶቹን በዚህ መልኩ አርሟል፡- ህግ-ወጥ የደመውዝ ተቀናሽ ለሆነባቸው ሰራተኞች መልሶ ለመክፍል በመስማማት፣ የሥራ ሰዓት መርሃ-ግብሩን በማሻሻል ሰራተኞቹ ሳምንታዊ የእረፍት ቀን እንዲያገኙ በማስቻል፣ የትርፍ ሰዓት በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን የሚያረጋግጥ ፖሊሲ በመቅረጽ፣ አማካሪ ቀጥሮ ስራ-አስኪያጆችን እና ተቆጣጣሪዎችን የቃላት ጥቃቶችን በማስወግድ ሰራተኞችን እንዴት የሚያበረታቱበት እና ለሥራ የሚያነሳሱበት ስልጠና እንዲያገኙ በማመቻቸት፣ የዓመታዊ ፍቃድ ገደቦችን በማስወገድ፣ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፊዴሬሽን ሰራተኞችን እንዲያገኝ በመፍቀድ እና የሙቀት መጠኑ ደህንነቱ ባልተጠበቀበት የፋብሪካው የልብስ ካውያ ክፍል ውስጥ የአየር ሙቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያ በመግጠም ናቸው።
ኬጂጂ አልባሳት
በኢትዮጵያ የዩንቨርስቲ አርማ ልብስ በሚያመርት ፋብሪካ ላይ የደረሱ የህግ ጥሰቶችን ለመፍታት የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ከዩኒቨርሲቲ ፍቃድ ካለው ካተር እና ባክ ከ1,300 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች ከአራት ወር በላይ ደሞዝ የሚሆን የክፍያ መጠን አስገኝቷል። የህግ ጥሰቱ - በህግ የተደነገገ የአገልግሎት ክፍያ እና የስራ ስንብት ጥቅማጥቅሞችን አለመክፈል - የተፈፀመው በአውሮፓውያን አቆጣጠር በጥቅምት 2021 ዓ.ም ሰራተኞቹን ከ135,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ ክፍያ ሳይፈጽም ስራ ባቆመው በኬጂጂ አልባሳት ኃ/የተ/የግ/ማ ነው፡፡
ጄፒ ጨርቃጨርቅ ኢትዮጵያ
ጄፒ ጨርቃጨርቅ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማ. (“ጄፒ”) የሚገኘው በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በትንሿ የደቡብዏ ከተማ ሐዋሳ ውስጥ ነው። በ40,000 ሜትር ስኩዌር ላይ የሚገኘው ጄፒ (ኢትዮጵያ) ጨርቃጨርቅ ኩባንያ፣ በቻይና፣ ባንግላዲሽ፣ ካምቦዲያ እና ቬየትናም ፋብሪካዎች ያሉት የቻይናው ኮንግላምሬት የውዢ ጂንማኦ ድርጅት አካል ነው፡፡ ፋብሪካው የዞኑ ብቸኛ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካን እንዲሁም የጥጥ ሸሚዞችን የሚያመርት የልብስ ማምረቻ ተቋሞችን ያጠቃልላል ይህም የሰራተኛ መብቶች ጥምረት የምርምር ርዕሰ ጉዳይ ነበር። ውዢ ጂንማኦ በ2019 ዓ.ም በፋብሪካው ከ2,500 እስከ 3,000 ሰራተኞችን ለመቅጠር በእቅድ ማስቀመጡ ተዘግቧል። የልብስ ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ ለፒቪኤች ያመርታል። የጨርቃጨርቅ ፋብሪካው በዞኑ ውስጥ ላሉ ፋብሪካዎች የጨርቃጨርቅ ምርት እንደሚያቀርብ ይታወቃል።
የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ሪፖርት በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ጥሰቶችን አግኝቷል፡-
- ደሞዝ እና ሰአታት
- የቅጥር ውል አለመስጠት
- የቅጣት ደመወዝ ቅነሳ/ያልተከፈለ የጉልበት ሥራ
- የክፍያ ሰነዶችን አለመስጠት
- ያልተቆራረጠ የምግብ መመገቢያ ጊዜ አለመስጠት
- በነፍሰ ጡር ሰራተኞች ላይ የሚደረግ መድልዎ
- ትንኮሳ እና ጥቃት
- የቃላት ጥቃት
ጄይ ጄይ ጨርቃጨርቅ
ጄይ ጄይ ጨርቃጨርቅ ("ጄይ ጄይ") በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ (ደረጃ 1) ውስጥ ይገኛል። 27,500 ካሬ ሜትር ቦታ ያለው የህንዱ ፋብሪካ በዞኑ ካሉት ትላልቅ ተቋማት አንዱ ነው። በልጆች አልባሳት ላይ የተካነ፣ ተቋሙ ለገርበር ችልድረን ዌር፣ ለችልድረንስ ፕሌስ፣ ለዊልያም ካርተር ኩባንያ እና ለኤች ኤንድ ኤም አልባሳት ልብሷችን ያመርታል።
የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ሪፖርት በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ጥሰቶችን አግኝቷል፡-
- ደሞዝ እና ሰአታት
- የቅጣት ደመወዝ ቅነሳ/ያልተከፈለ የጉልበት ሥራ
- የእረፍት እና የመመገቢያ ሰዓት አለመስጠት / ከስራ ሰዓት ውጭ ሥራ
- አስገዳጅ የትርፍ ሰዓት ስራ
- ትንኮሳ እና ጥቃት
- የቃላት ጥቃት
- የስራ ጤና እና ደህንነት
- ውስን የመጸዳጃ ቤት አገልግሎት
- ንጽህና የጎደለው የካፌቴሪያ ምግብ
አርቪንድ ላይፍ ስታይል አልባሳት ማኑፋክቸሪንግ
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኘው አርቪንድ ላይፍ ስታይል አልባሳት ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በህንዱ ዓለም አቀፍ አርቪንድ ላይፍ ስታይል አልባሳት ባለቤትነት ስር ከሚገኙት ሁለት የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ፋብሪካዎች አንዱ ነው። ከተቋሙ ገዢዎች ውስጥ ችልድረንስ ፕሌስ፣ ፒቪኤች፣ ኤች ኤንድ ኤም እና የገርበር የህጻናት ልብስ ይገኙበታል። ፋብሪካው በዋነኝነት የሚያመርተው ጂንስ፣ ሱሪ እና ሸሚዞችን ነው። (ሁለተኛው አርቪንድ ተቋም በሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በቅርቡ ሥራ ጀምሯል፤ የዚህ የሠራተኛ መብቶች ምርመራ ዘገባ አካል ያልሆነ ሲሆን ፣ በቅርብ ለኤች ኤንድ ኤም እና ፒቪኤች ዕቃዎችን አምርቷል።)
የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ሪፖርት በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ጥሰቶችን አግኝቷል፡
- የመደራጀት ነፃነት
- ደሞዝ እና ሰአታት
- የቅጣት ደመወዝ ቅነሳ/ያልተከፈለ የጉልበት ሥራ
- አስገዳጅ የትርፍ ሰዓት ስራ
- ያልተከፈለ የትርፍ ሰዓት ስራ
- ትንኮሳ እና ጥቃት
- የቃላት ጥቃት
- የስራ ጤና እና ደህንነት
- ራስን መሳት
- ያልተሟሉ የመጸዳጃ ቤት መገልገያዎች
ኤምኤኤ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ ከብር ኢንተርፕራይዞች
በትግራይ ሰሜናዊ አውራጃ በመቀሌ ከተማ የተመሰረተው ኤምኤኤ አልባሳት እና ጨርቃጨርቅ (ኤምኤኤ) እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 2016 ዓ.ም ላይ 1600 ሰራተኞች ቀጥሮ ያሰራ ነበር፡፡ በኢትዮጵ ውስጥ ከታች ወደ ላይ ከተዋቀሩት 17ቱ ፋብሪካዎች አንዱ የሆነው እና ባቤትነቱ የኢትዮጵያዊ ባለሀብት የሆነው ይህ ፋብሪካ የጥጥ ምርቶችን የመፍተል እና የመሸመን እንዲሁም ልብሶችን የመገጣጠም (መቁረጥ፤ መስራት እና መስፋት) አቅም ያለው ነው፡፡ የሚያመርታቸውም ምርቶች ሱሪዎችን፣ የውስጥ ሱሪዎችን፣ ሸሚዞች፣ ቲሸርቶችን እና የቤት ውስጥ ጨርቃ ጨርቅን ያጠቃልላል።
የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ሪፖርት በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ጥሰቶችን አግኝቷል፡-
- ደሞዝ እና ሰአታት
- የቅጣት ደመወዝ ቅነሳ/ያልተከፈለ የጉልበት ሥራ
- አስገዳጅ የትርፍ ሰዓት ስራ
- ያልተከፈለ የትርፍ ሰዓት እና መሰረት የሌላቸው የክፍያ ልማዶች
- በመመገቢያ ሰዓት ስራ ማሰራት
- ትንኮሳ እና ጥቃት
- ወሲባዊ ትንኮሳ
- ከእርግዝና ጋር የተያያዘ ትንኮሳ
- የቃላት ጥቃት
- የስራ ጤና እና ደህንነት
- ሠራተኞች በሥራ ወቅት መውደቅ
- ውስን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት
- ውስን የመጸዳጃ ቤት አገልግሎት